Silte Discussion Forum

Please login or register.

Login with username, password and session length
Advanced search  

News:

Author Topic: በደቡብ ክልል በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የአሳ ምርትን በዕጥፍ ለማሳደግ &  (Read 1893 times)

0 Members and 1 Guest are viewing this topic.

Shibal

  • Administrator
  • Sr. Member
  • *****
  • Posts: 324
በደቡብ ክልል በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት የአሳ ምርትን በዕጥፍ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው

 
አዋሳ ታህሳስ 8/2000/ዋኢማ/ በደቡብ ክልል በየዓመቱ እየተመረተ ያለውን 4ሺ 90 ቶን የዓሳ ምርት በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት በእጥፍ ለማሳደግ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ አስታወቀ ።በማኅበር ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ አሳ አስጋሪ ወጣቶችንና አርሶ አደሮች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል።


በቢሮው የአሳ ሃብት ልማትና ቁጥጥር ባለሙያ አቶ ላሎቶ ሶዶሬ ለዋልታ ኢንፎርሜሸን ማዕከል እንደገለጹት፤ በክልሉ ባለፈው ዓመት ለማዕከላዊ ገበያ የቀረበውን ከ4ሺ 90 ቶን በላይ አጥንቱ የወጣለትን ፍሌቶ አሳ ምርት በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ወደ 8ሺ 180 ቶን ለማሳደግ የሚያስችል ዕቅድ ወጥቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ ነው።


በአሳ አስጋሪ ማኅበራትና አሳ አምራች አርሶ አደሮች የሚመረተውን ይህንኑ የዓሳ ምርት በእጥፍ ለማሳደግ የሩዶልፍ ተፋሰስን ጨምሮ የአዋሳና አባያ ሐይቆችና በኦሞ ወንዝ አካባቢ የሚገኙ ስድስት ዓሳ አስጋሪ ማኅበራት ለታቀፉ 1ሺ 500 ወጣቶች ዘመናዊ መረብና የማስገሪያ ጀልባዎች በተመጣጣኝ ዋጋ በብድርና በሽያጭ እንደሚቀርቡ አስታውቀዋል።


ባለፉት አራት ዓመታት ቢሮው ከሰበታ የአሳ ምርምር ጋር በመተባበር ትንሹ አባያ እተባለ በሚጠራውና 23 ሄክታር በሚሸፍነው ውሃ 200 የአሳ ጫጩቶችን በማራባት ትረፋማ መሆን ለቻሉ 70 ያህል የላንፍሮና ስልጤ ወረዳ አርሶ አደሮች ማከፋፈሉን ገልፀዋል።

በተጨማሪም በአላባ ልዩ ወረዳ፣ በሲዳማ ፣ ጌዲዖና ጋሞጎፋ ዞኖች የተለያዩ አካባቢዎች ምርጥ የዓሳ ዝርያዎችን በማራባት ስራ ላይ ለሚሳተፉ አርሶ አደሮች የተለያዩ ግብዓቶችን ለማቅረብ የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስታውቀዋል ።


በክልሉ በማኅበር ተደራጅተው በአሳ ምርት ሥራ የተሳተፉ አሳ አሰጋሪ ወጣቶችና አንዳንድ የኩሬ አሳ አምራች አርሶ አደሮች ለገበያ ካቀረቡት የቆሮሶ ፣ ጥቁርና ነጭ የአሳ ዓይነቶች ሽያጭ በዓመት ከስምንት ሺ እስከ 11ሺ ብር የሚደርስ ገቢ በማግኘታቸው ኑሯቸው እየተሻሻለ መምጣቱን ባለሙያው አመልክተዋል።


በቀጣይም በጥናት ላይ የተመሠረተ ዘመናዊ የአሳ ምርት ሥራን በማስፋፋት ከዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በእንስሳት ምርምር ዳይሬክቶሬት ሥር የአሳ ምርምር ማዕከል እንደሚቋቋም መግለፃቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል ዘግቧል።
 

Source
Click here to register! 
Be as beneficent as the sun or the sea, but if your rights as a rational being are trenched on, die on the first inch of your territory.  ~Ralph Waldo Emerson
 

Page created in 0.23 seconds with 21 queries.